የአፍሪካ ቆነጃጅት የአድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ

You are currently viewing የአፍሪካ ቆነጃጅት የአድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ

AMN ሚያዝያ 15/2018 ዓ.ም

የአድዋ ድል መታሰቢያ የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ያለ ምንም የብሔር፤ ሃይማኖት፤ ቋንቋ፤ ጾታና መሰል ልዩነቶች ህብረብሔራዊ አንድነታቸዉን አክብረው፤ ለሃገራቸዉ አንድነትና ሉአላዊነት በጋራ የቆሙበትና፤ታላቅ ተጋድሎን የፈጸሙበት የጥቁር ህዝቦች ታሪክ የሚዘከርበት ማዕከል ነው፡፡

የአድዋ ድል መላዉ ኢትዮጵያዊያንን ብቻ ሳይሆን አፍሪካዊያንን ጭምር ያስተሳሰረና ልዩነትን አክብሮ በጋራ መቆም እንደሚቻል በተግባር ያስተማረ ድል ሲሆን የአድዋ ጀግኖችን ለመዘከር የተገነባዉ መታሰቢያም በሃገር ዉስጥ እና በውጭ ሃገራት ዜጎች ዘወትር ይጎበኛል፡፡

የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ከማሂ ኢቨንትስ ጋር በመተባበር በሚያዘጋጀው የ”Miss Africa Essence 2026″ የቁንጅና ውድድር ላይ ለመሳተፍ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ ቆነጃጅቶችም ይህንን ታሪካዊ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል፡፡

የአድዋ ድል የአፍሪካን ጥንካሬ ያስመሰከረ እና አፍሪካውያን አንድ ከሆኑ ማንኛውንም ፈተና ማሸነፍ እንደሚችሉ በተግባር ያረጋገጠ ድንቅ ታሪክ መሆኑን ቆነጃጅቶቹ መስክረዋል፡፡

ቆነጃጅቶቹ እንዳሉት ኢትዮጵያውያን ዘመናዊ ጦር መሳሪያ ከታጠቀው የውጭ ሃይል ጋር በጋሻና በጦር ብቻ ተጋጥመው ማሸነፋቸው ትልቅ መንፈሳዊና ታሪካዊ ትምህርት የሚሰጥ ነው ብለዋል፡፡

የአፍሪካን እምቅ ባህልና ተፈጥሮ ለተቀረው የዓለም ክፍል በማስተዋወቅ ረገድ ጉልህ ድርሻ ያለው ይህ ውድድር ብዙዎች የሚሳተፉበትና በአዲስ አበባ የሚካሄድ መሆኑን የአድዋ ድል መታሰቢያ ለኤኤምኤን የላከዉ መረጃ ያሳያል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review