የከተማ አስተዳደራችንን የ9 ወራት የሥራ አፈጻጸም ገምግመን ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ አጠናቀናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing የከተማ አስተዳደራችንን የ9 ወራት የሥራ አፈጻጸም ገምግመን ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ አጠናቀናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN ሚያዝያ 19/2018 ዓ.ም

በግምገማችንም ከአምስ አመት አንፃር የደረስንበት እያነፃፀርን ፣የተገኙ ውጤቶች እና ተስፋ ሰጪ አፈጻጸሞች እንዲሁም በቀጣይ መስተካከል ያለባቸው ተግባራት ለይተናል።

የ9 ወር አፈፃፀምን ጨምሮ ባለፋት አምስት አመታት ከተከናወኑ በርካታ ተግባራት ዋና ዋናዎቹን ለአብነት ያክል:-

• ስር የሰደዱ ኋላ ቀር አስተሳሰቦችን ችግሮችን ተጋፍጠን የጋራ እሴት ግንባታ ላይ በትጋት ሰርተናል።በዚህም አዲስ አበባን ከሰፈር ፖለቲካ አውጥተን፣ የዲፕሎማቲክ ማዕከልነቷ ይበልጥ ጎልብቶና አድጎ ከተማችን ከእኔነት ወደ የሁላችን ከተማነት ከፍ አድርገናታል።በዚህም ለኢትዮዽያዊን ብቻ ሳይሆን አፍሪካዊያን ሁሉ ዋና ከተማችን ብለዉ የሚኮሩባት ከተማ አድርገናታል።

• አዲስ አበባን “ እንደ ስሟ ውብ አዲስ አበባ “እናደርጋታለን ብለን በቃላችን መሰረት:-

• የከተማችንን ጎስቋላ ገጽታ ለመቀየር 74 በመቶ የሚሆነውን የጭቃ ቤት ወደ ውብ ምቹ ከተማ ለማድረግ በሰራነው ሥራ በ44 በመቶ በመቀነስ ችለናል።

• ተማሪዎቻችን የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም እና ዩኒፎርም የማቅረብ የትልድ ግንባታን አከናውነናል።

• የአዲስ አበባ ህጻናት ቦርቀዉ የሚጫወቱበት ከ5ሺህ በላይ የልጆች መጫወቻ ፣እንክብካቤ የሚያገኙበት ከ1000 በላይ ዴይ ኬር ገንብተን በርካታ ወላጆችን እፎይ አስብለናል።

• በከተማችን 30 የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላትን በመገንባት ጧሪ የሌላቸው አረጋውያን፣ አቅመ ደካሞች እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ወገኖቻችንን ተጠቃሚ አድርገናል።

• በ “የለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል” በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች ከአስከፊ ህይወት እንዲወጡና በተጨባጭ የሥራ ባለቤት እንዲሆኑ ተደርጓል።

• የአረጋዊያን መጦሪ ፣ መስማትና ማየት ለተሳናቸዉ ት/ቤት ተገንብተው ልማታችን ማንንም ወደ ኋላ የተወ እንመዳይሆን በጥቃቄ ሰርተናል።

• የተበከሉ ወንዞች ፀድዉ፣ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ እና በቆሸሹ የወንዝ ዳርቻ አካባቢዎች ይኖሩ ለነበሩ ነዋሪዎች የተሻለ መኖሪያ ቤቶች ተገንብተው ተሰጥቷል።

• ጨለማ የነበሩ ጐዳናዎች በርተዋል ። በዚህም ለወንጀል ለዝርፊያ ለአስገድዶ መድፈር አጋላጭ የነበሩ አካባቢዎች ተቀይረዋል።

• በየሜዳዉ ከመፀዳዳት ለህዝባችን ምቾትን የሚጨምሩና ክብርን የሚጠብቁ እንዲሁም ጤናው እንዲጠበቅ የሚያስችሉ ንጹህ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ መጸዳጃዎችን በስፋት ገንብተናል።

• የመገድ ሽፋንን 12.% ወደ20 % አሳድገናል።በርካታ የመኪና ማቆሚያዎች፣ ደረጃቸውን የጠበቁ መጸዳጃዎች፣ ሰፋፊ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች እና ማጣሪያ ማእከላት ተገንብተዋል።

• የከተማችንን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ከ70% በላይ ማሳደግ ችለናል።

የቤት አቅርቦት 480ሺ አድርሰናል ።

• ወጣቶች በአካል እና በአዕምሮ የዳበሩ እንዲሆኑ የስፖርት ማዘውተሪያ እና ደረጃቸውን የጠበቁ የስፖርት መወዳደሪያ ማዕከላት በየአካባቢዉ ገንብተናል።

• አዳዲስ ሆስፒታሎች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት ሲደረጉ፣ ነባሮቹም ታደሰው ደረጃውን ለጠበቀ አገልግሎት ዝግጁ ተደርገዋል።

• የከተማዋን የመንገድ እና የአረንጓዴ ስፍራ ሽፋን 2.8% ወደ24% አሳድገናል።

• ከአፍሪካ አስር ንጹህ ከተሞች አዲስ አበባ አንዷ ንጹህ ከተማ መሆን ችላለች።

•በዚህም የቱሪዝም ማዕከል በመሆን በ2018 ዘጠኝ ወራት ከ200 በላይ ዓለም አቀፍ ኮንፍራንሶችን አስተናግደናል።

አሁን ያገኘናቸውን ስኬቶች እና አፈጻጸም በቀጣይ የበለጠ በማጠናከር ከተማችንን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ መግባባት ላይ ደርሰናል።

• በህዝብ ተሳትፎ እና በመንግት በጀት ከ60ሺህ በላይ ፕሮጀክቶችን አጠናቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል።

• ከፍተኛ ተግዳሮት የሆነብንን ስር የሰደደ ቀርፋፋ የአገልግሎት አሰጣጥን እና የጉበኝነት ልምምድ ለመለወጥ የመንግስት አገልግሎቶችን በ6 የመሶም የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና በአንድ ዲጅታል ተንቀሳቃሽ የአውቶቡስ አገልግሎት መስጠት የቻልን ሲሆን፣ ቀሪ 5 ማልከላት በቅርቡ ወደ ስራ ይገባሉ።

• ልላኛዉ ተግዳሮት የሆነብንን የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ የገበያ ማዕከላትን እና የእሁድ ገበያዎችን በተለያዩ የከተማው አካባቢዎች አስፋፍተናል።

በመሆኑም በልማት፥በሰላም፥ በማህበራዊ ስራዎች አብሮን ሳይለየን የሰራውን መላው የከተማችን ነዋሪ በጣም እናመሰግናለን።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review