ወጣቶች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በነበራቸው ተሳትፎ ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ አበርክተዋል- የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን

You are currently viewing ወጣቶች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በነበራቸው ተሳትፎ ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ አበርክተዋል- የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን

AMN – ግንቦት 26/2018 ዓ.ም

ወጣቶች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በነበራቸው ተሳትፎ ለምርጫው ተዓማኒነት እና ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ አበርክተዋል ሲል የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን ገለጸ፡፡

ፌዴሬሽኑ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት በተሰጠው የታዛቢነት ኃላፊነት መሰረት በምርጫው አጠቃላይ ሂደት ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ተወካይ አሌክሳንደር ንጉሴ፤ በምርጫው የተወዳደሩ ፓርቲዎች በድህረ ምርጫ ወቅት ውጤትን በፀጋ በመቀበል ለወጣቶች አርአያ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል፡፡

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በአስተባባሪነት 2 ሺህ 500 ወጣቶች፣ በታዛቢነት 32 ሺህ 500 ወጣቶች መሳተፋቸውንም ተናግረዋል፡፡

ፌዴሬሽኑ ዜጎች በነፃነት ይበጀናል ላሉት የፖለቲካ ፓርቲ ድምጻቸውን እንደሰጡ መመልከቱንም ገልጿል፡፡

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የተወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎችም በድህረ ምርጫ ወቅት ውጤትን በፀጋ በመቀበል ለወጣቱ የማህበረሰብ ክፍል አርአያ ሊሆኑ እንደሚገባ በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

በየሻምበል ምህረት

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review