የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስና የቴክኖሎጂ ውድድር ተጀመረ

You are currently viewing የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስና የቴክኖሎጂ ውድድር ተጀመረ

AMN – ሰኔ 05/2018 ዓ.

የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ከ16 ዓለም አቀፍ ሀገራት የተውጣጡ ተሳታፊዎች የታደሙበትን የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ እና የቴክኖሎጂ ውድድር አስጀምሯል።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር በመርሐ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት ፤ ኮንፍረንሱ የፈጠራ ስራዎችን ለማበረታታት፣ የኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማነቃቃት፣ ልምድ ለመለዋወጥ እና ተጨባጭ የመፍትሄ ሀሳቦችን ለማፍለቅ ጉልህ ሚና ይጫወታል።

በመድረኩ 18 የምርምር ስራዎች ፣ 100 የፈጠራ ስራዎች እና 34 የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለዕይታ እንደሚቀርቡ ታውቋል።

የስራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኖሎጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ተሻለ በሬቻ በበኩላቸው፤ በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተከሰቱ ላሉ ችግሮች መፍትሄ የሚገኘው በመንግስት ጥረት ብቻ ሳይሆን፣ በወጣት ተመራማሪዎች እና በፈጠራ ባለሙያዎች የተቀናጀ ጥረት መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በዘመኑ የቴክኖሎጂ ዘርፍ የተካነ የሰው ኃይል ለመፍጠር ሰፊ የሪፎርም ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ለሚቀጥሉት ሶስት ቀናት በሚቆየው መድረክ ለተጨባጭ ችግሮች መፍትሄ የሚሆኑ የተሻሉ ሀሳቦች እንደሚፈልቁ እምነታቸውን ገልጸዋል።

ይህ መድረክ የኢንዱስትሪውን ዘርፍ በማዘመን እና የሀገር በቀል የቴክኖሎጂ አቅምን በመገንባት ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

በቤተልሔም አየነው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review