AMN – ሰኔ 22/2018 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኽ መሃሙድ ጋር በኢኮኖሚያዊ ትስስር፣ ደኅንነት እና የቀጠናዊ መረጋጋት ዙሪያ በመተማመንና በመከባበር ላይ የተመሠረተ የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ኢትዮጵያና ሶማሊያ ከድንበር በላይ የሚጋሩት ነገር አለ፤ እሱም እጅግ ውድ የሆነውን ህዝባችንን እና የጋራ እጣ ፈንታችንን ነው በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡