ኢትዮጵያ ማከናወኗን ቀጥላለች!

‎ዛሬ ያስመረቅነው የአርባምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት የ‘ገበታ ለትውልድ’ መርሃ-ግብራችን ያፈራው ሌላኛው ታላቅ ስኬት ነው። ይህ ዘመናዊ ሪዞርት ከ1,300 በላይ ሰዎችን የሚያስተናግድ የስብሰባ አዳራሽና በሐይቅ ላይ የተገነባ ልዩ ተንሳፋፊ ሬስቶራንትን ያካተተ ሲሆን፤ ከመዲናችን ባሻገር የኮንፈረንስ ቱሪዝምን በማስፋፋት ኢትዮጵያን የዓለም አቀፍ መድረኮች ማዕከል የማድረግ ርዕያችንን ያጠናክራል፤ ለአካባቢው ማኅበረሰብም ሰፊ የሥራ ዕድል ፈጥሯል።

‎መላው የሀገራችን ሕዝብ፣ ዳያስፖራውና የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ይህንን አዲስ የሀገራችንን ዕንቁ ስፍራ በመጎብኘትና በመጠቀም፣ የኢትዮጵያን አዲስ የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ምዕራፍ በጋራ እንድንቋደስ ጥሪዬን አቀርባለሁ! – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ/ር)

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review