” ማሰሻ ” አዲስ የቴሌቭዥን መዝናኛ ዝግጅት በኤ.ኤም.ኤን ሊቀርብ ነው

AMN ሐምሌ 11/2018

በአርቲስት ትእግስት ግርማ ተዘጋጅቶ የሚቀርበው ማሰሻ የተሰኘው የቴሌቭዥን መዝናኛ ዝግጅት በቅርቡ በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እንደሚቀርብ ተገለጸ።

የቴሌቭዥን መዝናኛ ዝግጅቱ ማብሰሪያ መርሃ ግብር አርቲስት ትእግስት ግርማ እና የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የገበያ ልማት ዘርፍ ም/ስራ አስፈፃሚ አቶ መሀመድ ናስርን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና ታዋቂ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በተገኙበት ተካሂዷል።

ማሰሻ የቴሌቪዥን መዝናኛ ዝግጅት በዋናነት ወጣቶች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚቀርብ ዝግጅት ሲሆን በቅርቡ በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ መተላለፍ ይጀምራል።

በዮሀንስ አዳነ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review