በአዲስ አበባ የሕጻናትን ዕድገትና ደህንነት ለማረጋገጥ የተሰሩ ስራዎች የብዙዎችን ትኩረት ስበዋል

You are currently viewing በአዲስ አበባ የሕጻናትን ዕድገትና ደህንነት ለማረጋገጥ የተሰሩ ስራዎች የብዙዎችን ትኩረት ስበዋል

AMN- ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም

በመዲናዋ በማህበራዊ አገልግሎት እና በሕጻናት ተኮር ልማት ላይ የተሰሩ ስራዎች የብዙዎችን ትኩረት ስበዋል።

አዲስ አበባን ለሕጻናትና ታዳጊዎች ምቹ፣ ደህንነቷ የተጠበቀች እና ማራኪ የዕድገት ማዕከል ለማድረግ በሰፊው እየተሰራ ነው፡፡

ከተማዋን ከአየር ንብረት ተጽዕኖ መከላከልና የከተማዋን ስነ-ምህዳር ማሻሻል ላይ ያተኮሩት የልማት ስራዎች ለዚህ ታላቅ ስኬት ትልቅ መሠረት በመጣል ላይ ናቸው።

የከተማ አስተዳደሩ እና ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረት ማሳያ የሆኑት መርሃ ግብሮች፤ ለከተማዋ እድገት እና ለህጻናት የተሻለ ኑሮ መረጋገጥ የጎላ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ።

በተለይም በማህበራዊ አገልግሎቶችና በሕጻናት ተኮር ልማቶች ላይ የተሰሩት ስራዎች የብዙዎችን ትኩረት ስበዋል።

በከተማዋ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተከናወኑት የአረንጓዴ ልማት ስራዎች ለሕጻናት እና ወጣቶች ጤናማ አካባቢን በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛል። ይህ ደግሞ ሕጻናት በአካልና በአዕምሮ ጤናማ ሆነው እንዲያድጉ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል።

በአዲስ አበባ እየተከናወኑ ያሉ የከተማ ልማትና የዲጂታል አሰራር ማሻሻያዎች የሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን የውጭ ባለሙያዎችንና ተቋማትን ትኩረት በመሳብ ላይ ይገኛሉ። ይህም ከተማዋ ለሌሎች ሃገራት ከተሞች ምሳሌ የምትሆንበትን ዕድል እየፈጠረላት ይገኛል።

የልማት ስራዎቹ ትኩረት ያደረጉት ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገን በማሰብ ለህጻናትና ለወጣቱ ትውልድ የተሻለች፣ ሰላማዊትና ምቹ የኢኮኖሚ እንዲሁም የማህበራዊ መሠረት ያላት ከተማን አስረክቦ ማለፍ ላይ ነው። የወደፊቱ ትውልድ ዕጣ ፈንታ ከዚህ አወንታዊ ጅምር ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው።

እነዚህ የልማት ስራዎች የህጻናትን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ከፍ የሚያደርጉ፣ የዙጎችን አኗኗር የሚያሻሽሉ እና ዘላቂ ሰላምና ልማት የሚያረጋግጡ ምዕራፎች ናቸው።

ለህጻናት እድገት ምቹ የሆኑ አካባቢዎችን ማስፋፋትና የነገን ሀገር ተረካቢዎችን ለማነጽ የተጀመሩት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

የተከናወኑት ስራዎች ውጤት የአንድ ወቅት ስኬት ብቻ ሳይሆኑ የረጅም ጊዜ ራዕይን ያነገቡ በመሆናቸው ለቀጣይ ዘላቂ ልማት ትልቅ ዋስትና ይሰጣሉ።

በወርቅነህ አቢዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review