ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከጋና ፕሬዚዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ ጋር ተወያዩ

You are currently viewing ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከጋና ፕሬዚዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ ጋር ተወያዩ

AMN- ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም

ከአፍሪካ ኅብረት የጤና ዘርፍ ልዩ የመሪዎች የጤና ጉባኤ በተጓዳኝ፣ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከጋና ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ ጋር በጁብሊ ሀውስ በሁለትዮሽ እና በጋራ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ኢትዮጵያ ከጋና ጋር ከፓን-አፍሪካኒዝም ንቅናቄ መነሻ ጀምሮ ለዘለቀው ታሪካዊና ጠንካራ የዲፕሎማሲ ግንኙነቷ ትልቅ ሥፍራ የምትሰጥ መሆኑን ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ የሚገኘው አዲሱ የጋና ኤምባሲ ሕንፃ መጠናቀቅም የሁለቱ ሀገራት የማይናወጥ ወዳጅነት ምልክት መሆኑን በውይይታቸው መነሳቱን ጠቁመዋል።

ፕሬዚዳንት ማሃማ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነፃነትና የአንድነት አርማነቷን እንደጠበቀች፣ አሁን ደግሞ በአረንጓዴ አሻራና በሌሎች የልማት ዘርፎች እያሰመዘገበቻቸው ባሉ አበረታች ለውጦች እና ስኬቶች በእጅጉ መደነቃቸውን ገልጸውልኛል ብለዋል።

በተጨማሪም ፕሬዚዳንቱ ሀገራችን ለ12ኛ ጊዜ የሚካሄደውን የጣና ፎረም ለማዘጋጀት እያከናወነችው ያለችውን የቅድመ ዝግጅት ስራ የሚበረታታ መሆኑን አንስተዋል።

በፎረሙ ቦርድ ላይ እያበረከቱ ላሉት እጅግ የላቀ አመራርም የከበረ ምስጋና መቅረቡ ተገልጿል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review