ለአረንጓዴዋ ኢትዮጵያ፤ በአንድ ጀምበር 8 መቶ ሚሊዮን ችግኞች ይተከላሉ

You are currently viewing ለአረንጓዴዋ ኢትዮጵያ፤ በአንድ ጀምበር 8 መቶ ሚሊዮን ችግኞች ይተከላሉ

AMN- ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ አዲስ ታሪክ የሚጽፍ ታላቅና አስደናቂ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር እያካሄደች ትገኛለች።

በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በአንድ ጀምበር ብቻ 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል የተያዘው ግብ፣ የሀገራችንን የተፈጥሮ ሀብት የመንከባከብና የአየር ንብረት ለውጥን የመከላከል ቁርጠኝነት በግልጽ የሚያሳይ ነው።

መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ ወጣቶች፣ አረጋውያን፣ የመንግሥትና የግል ተቋማት ከጫፍ እስከ ጫፍ አንድ ላይ በመሰለፍ የታሪክ አካል እየሆኑ ይገኛሉ።

ዛሬ የምትተከለው እያንዳንዷ ችግኝ ለምግብ ዋስትና፣ ለውሃ ሀብት ጥበቃ፣ ለምግብ አቅርቦትና ለቀጣይ ትውልድ ንጹህ አየር ዋስትና ናት።

ዛሬ የምንተክለው ችግኝ፣ ነገ የምንሰበስበው አረንጓዴ ተስፋ ነው።

የትም ይሁኑ የት፣ በሚኖሩበትና በሚሠሩበት አካባቢ ቢያንስ አንድ ችግኝ በመትከል የዚህ ታሪካዊ ዕለት አካል ይሁኑ።

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review