ሁለት ሚሊየን ብር የሚያሸልም የፉትሳል ውድድር በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

You are currently viewing ሁለት ሚሊየን ብር የሚያሸልም የፉትሳል ውድድር በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

AMN-ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ስፖርት ለሁሉም ከኢግል አይ ኮሚኒኬሽን ጋር በመተባበር ሁለት ሚሊየን ብር የሚያሸልም የፉትሳል ውድድር ሊያካሂዱ ነው።

ወድድሩን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ፅ/ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።

በመግለጫው የቢሮው የስፖርት ማደራጃ እና ውድድር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አያሌው ታደለ ፣ የኢግል አይ ኮሚኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ብሩክ አሰግድ እና የስፖርት ለሁሉም አመራሮች ተገኝተዋል።

አቶ አያሌው ውድድሩ ለወጣቶች የመዝናኛ አማራጭ እና የተሳትፎ እድል እንዲሰጥ ታስቦ እንደተዘጋጀ ገልጸዋል።

አቶ ብሩክ በበኩላቸው ኅብረተሰቡን አሳታፊ ለማድረግ እና አዲስ አበባ ከተማን የበለጠ ለማስተዋወቅ አላማ አድርጎ እንደሚከናወን ጠቁመዋል።

ውድድሩ 100 ቡድኖች እንደሚሳተፉበት በመግለጫው ተጠቅሷል።

ጨዋታዎቹ በ11ዱም ክፍለከተሞች በሚገኙ የተመረጡ የስፖርት ማዝወተሪያ ስፍራዎች ላይ ይከናወናሉ።

መስከረም 23፣ 2019ዓ.ም እንደሚጀምር የተጠቆመው ውድድር ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ቡድኖች መመዝገቢያ 40 ሺ ብር ከፍለው መወዳደር እንደሚችሉ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ስፖርት ለሁሉም ከኢግል አይ ኮሚኒኬሽን ጋር በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድም ተፈራርመዋል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review