ከብሄርና ከሐይማኖት ግጭቶችና ከንብረት ውድመት በስተጀርባ ያሉት ድብቅ እጆች

You are currently viewing ከብሄርና ከሐይማኖት ግጭቶችና ከንብረት ውድመት በስተጀርባ ያሉት ድብቅ እጆች
  • Post category:ፖለቲካ

AMN- መስከረም 13/2019 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የበርካታ ብሄር ብሄረሰቦች እና ሐይማኖቶች መገኛ ስትሆን፤ ህዝቦቿም ተከባብረውና ተቻችለው በመኖር የሚታወቁ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያዊያን በመካከላቸው ልዩነቶችና አለመግባባቶች ቢፈጠሩ እንኳ እንደ ወንድማማች ህዝቦች በንግግር፤ በምክክር እና በሽምግልና የመፍታት ባህል ያላቸው ደጋግ ህዝቦች ናቸው፡፡

ኢትዮጵያዊያን ይህንን የመሰለ መልካም እሴት ያላቸው ህዝቦች ቢሆኑም በብሄር ስም የሚታገሉና የግብጽን የጥፋት ተልእኮ የተቀበሉ ጽንፈኛ ሃይሎች ግን በወንድማማች ህዝቦች መካከል ጥላቻንና ግጭትን በመፍጠር ኢትዮጵያዊያን እርስ በርስ እንዲጠፋፉ ብዙ አሲረዋል።

በተለይ የግብጽና የሻዕቢያ ተላላኪ የሆኑት እንደ ህገወጡ የህወሃት ቡድን: ሸኔና ፋኖ ያሉ ጽንፈኛ ቡድኖች ከኢትዮጵያዊነት ስነ ልቦና፤ ባህልና ሐይማኖት ባፈነገጠ መንገድበንጹሃን ዜጎች ላይ የተለያዩ ጥቃቶችን ሲፈጽሙ ቆይተዋል።

ራሳቸዉ ሆን ብለዉ በሚፈጸሙት ወንጀል ጠላትህ እከሌ የሚባለዉ ብሄርና ሃይማኖት ነዉ: ተደራጅተህ አጥፋዉ በማለት በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎችና ተቀላቢ አክቲቪስቶቻቸዉ በወንድማማች ህዝቦች መካከል የጥፋትና የዕልቂት ቅስቀሳዎችን በተደጋጋሚ አስተጋብተዋል።

የጥፋት ሃይሎቹ በግብጽ ድጋፍና በሻዕቢያ አስተባባሪነት ጽምዶ የተሰኘ የጥፋት ግንባር በመፍጠር በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የእምነት ተቋማትን አቃጥለዋል፤ መሰረተ ልማቶችንም አውድመዋል፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ጨምሮ ግዙፍ ሃገራዊ ፕሮጀክቶችን በማደናቀፍ ቀንደኛ የኢትዮጵያ ጠላት መሆናቸዉን በተግባር አረጋግጠዋል።

ህገወጡ የህወሃት ቡድን: ሸኔ: ፋኖና ሌሎች ጽንፈኛ ሃይሎች የጋራ ጥምረት በመፍጠር ተማሪዎች እንዳይማሩ፤ አርሶ አደሮች እንዳያርሱ፤ የህክምና ተቋማት አገልግሎት እንዳይሰጡ፤ አምራች ኢንዱስትሪዎች እንዳያመርቱ እንቅፋት በመሆን ኢትዮጵያ ከድህነት አረንቋ እንዳትወጣ የተቻላቸዉን ሁሉ አድርገዋል።

የሃገሪቱን የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎችንና የንግድ ሥርዓቶችን በማስተጓጎል ህዝቡ በኑሮ ዉድነት እንሰቃይና በመንግስት ላይ እንዲያምጽ በርካታ ደባዎችን ፈጽመዋል።

አንዳንድ የቀበሌና የወረዳ የጸጥታ ተቋማትን ጨምሮ በየደረጃዉ የሚገኙ የመንግስት አደረጃጀቶችን በማፍረስ በሃገሪቱ ሥርዓት አልበኝነት: ዉንብድና: ዝርፊያና የእርስ በርስ ግድያ እንዲፋፋም በርካታ የጥፋት ተግባራትን ፈጽመዋል።

ከሻዕቢያ ጋር ግንባር በመፍጠር ኢትዮጵያን የባህር በር ያሳጣዉ ህገወጡ የህወሓት ቡድን ሸኔና ፋኖን ከጀርባ ሆኖ ለጥፋት ከማስተባበሩም በላይ ከትናንትናዉ ስህተቱ ሳይማር ህገመንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል ለመናድ በሃገሪቱ ላይ ተደጋጋሚ ጦርነቶችን ከፍቷል።

በሰሜኑ ጦርነትም ለህይወት መጥፋትና ለንብረት መውደም ትልቅ ምክንያት ሆኗል፡፡

በጦርነቱ ተሸንፎ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ከፈረመ በኋላም የገባዉን ቃል አፍርሶ ከሻዕቢያና ግብጽ ጎን ተሰልፎ ኢትዮጵያ ለመዉጋት ተደጋጋሚ ትንኮሳዎችን በመፈጸም ላይ ይገኛል።

ህገወጡ ቡድን ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ተባብሮ ኢትዮጵያን የማፍረስ ህልሙን ለማሳካት ጽምዶ የሚባል ጥምረት መመስረቱንም በቅርቡ ይፋ አድርጓል።

ሻዕቢያና ህገወጡ የህወሃት ቡድንን ጨምሮ ፋኖና ሸኔን የመሠሉ ጽንፈኛ ሃይሎች ኢትዮጵያን ለማፍረስ ያላቸዉን ተልዕኮ ጠንቅቀዉ የተረዱት የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ሃይማኖቶች ወንድማማችነታቸውንና አንድነታቸውን በማጠናከር የግብጾችን እኩይ አላማ በጽናት አክሽፈዋል።

ከሃገር መከላከያ ሰራዊትና ከሌሎች የጸጥታና ደህንነት ሃይሎች ጋር በመተባበርም የፈርዖኖቹንና የተላላኪዎቻቸውን የጥፋት ተልእኮ በጽናት መክተዋል።

በኢትዮጵያ ህልዉናና ሉዓላዊነት ላይ የማይደራደሩት ኢትዮጵያዊያን ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በጋራ እዉን እንዳደረጉት ሁሉ በግብጽ: በሻዕቢያ በህወሃት ምክንያት ያጡትን የባህር በር ለመመለስም በአለም አደባባይ ድምጻቸዉን በማሰማት ላይ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ የፈርዖኖቹን የጥፋት ሴራ አክሽፋ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን እንደገነባችዉ ሁሉ የባህር በር ፍላጎቷን በቅርቡ ታሳካለች ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review