ከስድስት ሚሊዮን ብር በላይ አታለው የተቀበሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

You are currently viewing ከስድስት ሚሊዮን ብር በላይ አታለው የተቀበሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

AMN – የካቲት 15/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበበ ከተማ አስተዳዳር መሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ ሰራተኞች ነን፣ አመራሮችን እናውቃለን፣ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እናሰራላችኋለን በማለት 6,360,259.09 (ስድስት ሚሊዮን ሶስት መቶ ስልሳ ሺ ሁለት መቶ ሃምሳ ዘጠኝ ) ብር አታለው የተቀበሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

1. ቶማስ ማናዬ ተበጀ

2. ሳሙኤል ኪዳኔ ኃይሌ

3. ጽዮን አበራ ጣፋ

4. ዳዊት መንግሰቱ

5. ሚኪያስ አውላቸው

የተባሉ ግለሰቦች በ2017 ዓ.ም በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 አስተዳዳር ክልል ውስጥ የግል ተበዳይ አቶ መሬት ስፋ 3,825 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የከብት ማደለቢያ አገልግሎት ለማዋል የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በመሰራት ሒደት ላይ ያለ መሆኑን መረጃ ያገኛሉ።

ወዲያውም “እኛ የመሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ አመራር ሹፌር እና ጸሐፊ ነን፤ አብረናቸዉ ነው የምንሰራዉ፣ ካርታ በአስቸኳይ እናስጨርሳለን” በማለት 6,360,259.09 (ስድስት ሚሊየን ሶስት መቶ ስልሳ ሺ ሁለት መቶ ሃምሳ ዘጠኝ) ብር አታለው ተቀብለዋል።

ገንዘቡን ከተቀበሉ በኋላ ከአካባቢው ቢሰወሩም ፖሊስ የቀረበለትን ጥቆማ መሠረት በማድረግ ባደረገው ክትትል ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር አውሎ በ12/06/2018 ዓ.ም ፍርድ ቤት ማቅረቡን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review