መጋቢት 24 ለኢትዮጵያ አዲስ የለውጥ ብስራት ያበሰረበት የለውጥ ጅማሮ ዕለት ነው

You are currently viewing መጋቢት 24 ለኢትዮጵያ አዲስ የለውጥ ብስራት ያበሰረበት የለውጥ ጅማሮ ዕለት ነው

AMN – መጋቢት 24/2018 ዓ.ም

መጋቢት 24 በኢትዮጵያ ከ8 ዓመት በፊት የነበረው የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና የፓለቲካ ስብራቶችን ለማከም የለውጡ መንግስት ወደ ስልጣን ብቅ ያለበት ነበር።

ታድያ ባለፉት ስምንት ዓመታት በተጨባጭ የተመዘገቡ ሰው ተኮር የሆኑ ሁሉን አቀፍ የልማት መስኮች የህዝቡ ድጋፍ እንዲቸራቸው አድርጓል።

የልማት ስራዎቹ የህዝቡን ችግር ከመፍታት ባለፈ ለዘመናት ስሟና ግብሯ ሳይመሳሰል የነበረችው አዲስ አበባ ከተማ የለውጥ ሀዋርያ በመሆን ምቹና የዘመነች ከተማ መሆን ጀምራለች።

እናም በዛሬው እለት ብርድና ውርጩ ያልበገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች የተመዘገቡ ለውጦችና ስኬቶችን ለማጽናት ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በመደረግ ላይ ናቸው።

በጉለሌ ክፍለ ከተማም ከመጋቢት 2010 ጀምሮ እንደ ሀገር የተጀመሩ ጉልህ የለውጥ ስራዎች ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በሚል የድጋፍ ሰልፍ በማድረግ ላይ ናቸው።

በመርሐ ግብሩም የተለያዩ መልዕክቶች በመተላለፍ ላይ ይገኛሉ።

በደሴ ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review