AMN-ሚያዚያ 11/2018 ዓ.ም
በባዶ እግር ታሪክን ከመስራት ጀምሮ በአለም አደባባይ ሰንደቅ ዓላማን ከፍ ያደረጉ ብርቅየ አትሌቶች መገኛዋ ኢትዮጵያ አሁን ላይ ታሪክን በመዘከር እና አዳዲስ ታሪኮችን በመፃፍ ላይ ትገኛለች፡፡
አዲስ አበባ ከተማ በልማቶቿ የአለም ድንቅ የሀገርም ኩራት የሆኑ አትሌቶችን አንድም ትዘክራለች በሌላ መልኩም በህይዎት እያሉ ታመሰግናለች፡፡
ለዚህ ደግሞ ትክክለኛ ማሳያዉ አዲስ ስፖርት ፓርክ ነዉ፡፡
ፓርኩ የትናንት ትውልዶችን የሚዘክር የዛሬ ትውልድ የትናንት ትዉልድን ገድል ተመልክቶ ዛሬ ላይ የራሱን ታሪክ ይፅፍ ዘንድም የሚያስችል ነዉ፡፡
አዲስ አበባ ከተማ የስፖርት ቱሪዝም መናገሻ ለመሆን በሰራችዉ ስራ እና ባስመገበችዉ ድል የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የአንድ ቀን ሩጫ የአዲስ አበባ ግራንድ ፕሪ ዉድድርን ማሰናገድ ችላለች፡፡

የአለም ስመ ጥር የትራክ ኮኮቦችም የአዲስ ስፖርት ፓርክን ጎብኝተዋል፡፡ እነሱም የትናንት እና የዛሬ ትዉልድ ድንቅ ኢትዮጵያዊያንን አስተዉለዋል፡፡ በመዲናዋ ልማትም መደመማቸዉን ገልፀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ልማትና ለስፖርቱ ዘርፍ የተሰጠ ትኩረት ለሌሎች ሀገራትም ልምድናተሞክሮ የሚቀመርባቸዉ ስለመሆኑ ገልፀዋል፡፡
የዉበት ማሳያዉ አራዳ ፓርክ የታሪክ ማህደሩ የአደዋ ድል መታሰቢያም በአትሌቶቹ መጐብኝቱን የከንቲባ ፅሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡