AMN ሚያዝያ 16/2018
ስዊዲን በሁለትዮሽ እና ባለብዙወገን ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር የበለጠ ማጠናከር እንደምትፈልግ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞትዎስ (ዶ/ር) ከስዊድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪያ ማልመር ስቴነርጋርድ ጋር በስቶኮልም ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም፤ በአፍሪካ ቀንድ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።
በዚሁ ወቅትም ሀገራቱ ታሪካዊ እና ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ግንኙነት እንዳላቸው ያወሱት ሚኒስትሩ፤ ወዳጅነቱን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
የሀገራቱን ግንኙነት በንግድና ኢንቨስትመንት ረገድ የበለጠ ማጠናከር እንደሚያስፈልግም ነው ያመላከቱት።

የስዊዲን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተፈጠረው ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድል እንዲጠቀሙም ጥሪ አቅርበዋል።
የስዊዲን አቻቸው በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያና ስዊድን ግንኙነት ጠንካራ መሆኑን ተናግረዋል።
ስዊዲን በሁለትዮሽ እና ባለብዙወገን ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር የበለጠ ማጠናከር ትፈልጋለች ብለዋል።