ህዝብ ቤቱ የቀረ እስከማይመስል ድረስ ገና ጐህ ሳይቀድ ወደ መስቀል አደባባይ በመትመም በሚገርም ስሜትና በደስታ እየጨፈረ ድጋፉን ገልፆልናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing ህዝብ ቤቱ የቀረ እስከማይመስል ድረስ ገና ጐህ ሳይቀድ ወደ መስቀል አደባባይ በመትመም በሚገርም ስሜትና በደስታ እየጨፈረ ድጋፉን ገልፆልናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN ግንቦት 18/2018 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የዛሬዉ በጣም ልዩ ነዉ በሚል መሪ ሃሳብ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ህዝብ ቤቱ የቀረ እስከማይመስል ድረስ ገና ጐህ ሳይቀድ ወደ መስቀል አደባባይ በመትመም በሚገርም ስሜትና በደስታ እየጨፈረ ድጋፉን ገልፆልናል ብለዋል፡፡

ይህ የድጋፍ ሰልፍና የምረጡኝ ቅስቀሳ የማጠቃለያ መርሀግብር ነዉ። ልትደግፉን፥ ልታበረታቱን እንቅልፋችሁን ትታችሁ በለሊት ወደ መስቀል አደባባይ ለተመማችሁ ወድ የከተማችን ነዋሪዎች በራሴና በፓርቲዬ ብልፅግና ስም እጅግ አድርጌ አመሰግናሁ! እናከብራችኋለን !! ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ለዓለም አንድ ታላቅ መልዕክት አስተላልፋችኋል፥ ኢትዮጵያውያን በምርጫ ብቻ እንደሚያምኑና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት እንደሚችሉ ፥መንግስትን በምርጫ፣ በህዝብ ይሁንታ ማፅናት የሚችሉ ብርቱ ህዝቦች መሆናችንን ለዓለም ያረጋገጥንበት በመሆኑ አዎን ክብር ይገባችኋል።

በምርጫ ድምፅ የመስጠት ሂደት ብቻ ሳይሆን ይልቁንም የተረጋጋ የፖለቲካ ሥርዓት የማፅናት ፥ ዘላቂ ሰላምን የማረጋገጥ ፥ የተጀመሩትን የልማት ስራዎች የማስቀጠል ፅኑ መንገድ እና ሂደት ነው ።

ስልጣን በምርጫ እንጂ በጉልበት ወይም እንደቅርጫ የሚከፋፈል አይደለም፥ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት የምናፀናበት ህዝባችን የሉዓላዊ ስልጣን ባለቤት መሆኑን የምናስመሰክርበት ነው ብለዋል፡፡

የፓለቲካ ስልጣን ከህዝብ ይሁንታ ውጭ ሊሳካ አይገባዉም፥ ዳግም ምረጡን ብለን በብዙ የምንጐተጉታችሁ ከእናንተ ድምፅ ውጭ ወደሥልጣን የምንመጣበት ሌላ መንገድ እንደሌላ ሥለምናምን ነው።

በመሆኑም 7ኛውን ምርጫ ዴሜክራሲያዊ፥ ሰላማዊ፥ ፍትሃዊ ተዓማኒ ማድረግ አንዱና ዋናው ግባችን ነው ።

እስከ አሁን ባለው ጉዟችን ብልፅግና ፓርቲ ብቻ ሳይሆን ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ስልጣን የሚመነጨው ከህዝብ ይሁንታ መሆኑን በማመን ሃሳባቸውን በሰላማዊ መንገድ በማራመድ፥ በመከራከር እና ክርክሩን ዉድድሩን ለህዝብ ያደረሳችሁ ሚዲያዎች ሁሉ በአጠቃላይ ስልጣን ከህዝብ ድምፅ ብቻ እንዲሆን ፅኑ የዴሞክራስያዊ ስርዓት ለመገንባት የሰራችሁ ሁሉ ታላቅ ክብር ይገባቸዋል።

እስከ አሁን ሃሳባችን ገልፀን ተከራክረናል፥ በሃሳብ ሞግተናል፥ ህዝባችን አዳምጦናል፤ ከዚህ በኋላ

ህዝባችን ጥሩ ዳኛ እንደሆነ አምነን በፅናት እንዲወስን እንጠብቀው።

እስከ ዛሬ በሃሳባችሁ፥ በጉልበታችሁ በገንዘባቸሁ፥ በእውቀታችሁ በጉዟችን ሁሉ ደግፋችሁናል ፥ አብራችሁን ለነበራችሁ የከተማችን ነዋሪዎች ከልብ እናመሰግናለን!

መንገዳችን መደመር ነው፥ መዳረሻችን ብልፅግና ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review