በመዲናዋ የተለያዩ ወንጀሎችን እና የጸጥታ ስጋቶችን ቀድሞ በመከላከል ረገድ የተገኙ ዉጤቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል – የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ

You are currently viewing በመዲናዋ የተለያዩ ወንጀሎችን እና የጸጥታ ስጋቶችን ቀድሞ በመከላከል ረገድ የተገኙ ዉጤቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል – የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ

AMN- ግንቦት 18/2018 ዓ.ም

በመዲናዋ የተለያዩ ወንጀሎችን እና የጸጥታ ስጋቶችን ቀድሞ በመከላከል ረገድ የተገኙ ዉጤቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ገለጸ።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ፣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ እና በሸገር ከተማ በሙዳ ፉሪ የምሽት አንድ ማዕከል ስምሪት ለአዲስ ከተማ ፖሊስ ፣ ለጋቸና ሲርና ህዝባዊ አደረጃጀቶች ፣ ለደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች እና ሠላም ሠራዊት የፀጥታ አደረጃጀቶች በጥምር በተገኙበት የምሽት ስምሪት ተሰጥቷል።

የጋራ ስምሪቱ በሁሉም ክፍለ ከተሞች መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያጠናክር እና ወንጀሎችን ቀድሞ ለመከላከል የሚያግዝ ስለመሆኑ ተመላክቷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በከተማዋ ጨለማን ተገን ተደርጎ የሚከናወኑ ወንጀሎችን ለመቀነስ የተጀመሩ የፀጥታና የደህንነት ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አራጌ እሸቴ የፖሊስ ሃይል ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የፀጥታ ስጋቶችን ቀድሞ በመለየት የቅድመ ምርጫ እና ድህረ-ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን በትጋት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፤ ተአማኒና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ተልዕኳቸውን በብቃት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን የጥምር የፀጥታ መዋቅር አባላት ለኤ ኤም ኤን ተናግረዋል ።

መሐመድኑር ዓሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review