AMN ግንቦት 18/2018 ዓ.ም

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለ1447ኛው ለዒድ አል አድሐ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ሙሉ ቃል ቀጥሎ ቀርቧል፡-
እንኳን ለ1 ሺህ 447ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ።
የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል ተፈትኖ የመሻገር፣ የመታዘዝ እና የመሥዋዕትነት በዓል ነው። ነቢዩ ኢብራሂም በአላህ ትእዛዝ ልጃቸውን ለመሥዋዕትነት ያዘጋጁበት፤ ጽናታቸው ተፈትኖም ያሸነፉበት ታላቅ በዓል ነው፡፡
በዓሉን ስናከብር ቅንነትን፣ መልካምነትን፣ መታዘዝን፣ በጎ አድራጊነትንና ትኅትናን በሕይወታችን ተግባራዊ በማድረግ ሊሆን ይገባል።
በተመሳሳይ መልኩ ሀገር የምትጸናው በመሥዋዕትነትና በትውልድ ቅብብሎሽ በሚከፈል ዋጋ መሆኑን በመገንዘብ ለምንወዳት ሀገራችን ኢትዮጵያ ከልብ በሆነ ፍቅር አስፈላጊውን ዋጋ በመክፈል ማጽናት እና ማሻገር ከሁላችንም ይጠበቃል።
በዓሉ በሀገራዊ ምርጫ መዳረሻ የሚከበር ነው። መላው ሕዝበ ሙስሊም በመጪው ምርጫ በመሳተፋ ሀገረ መንግሥት የማጽናት ታሪኩን እንዲያስቀጥል አደራ እላለሁ።
መልካም የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል!
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ