በመደመር መጽሐፍ ሽያጭ የተገነባው በያቤሎ ከተማ የሚገኘው የቦረና ባሕል ማዕከል ተመረቀ

AMN – ግንቦት 19/2018 ዓ.ም

በያቤሎ ከተማ የሚገኘው የቦረና ባሕል ማዕከል ዛሬ መመረቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፣ በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በ2013 ዓ.ም የመሰረት ድንጋይ ተቀምጦለት የነበረውና ዛሬ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው የባህል ማዕከል፤ በመደመር መጽሐፍ ሽያጭ የተገነባ ሲሆን በ57.6 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ነው ብለዋል።

ማዕከሉ የገዳን ሥርዓት ለማሳየት በልዩ ሁኔታ ዲዛይን የተደረገ ሲሆን በአንድ ጊዜ እስከ 2ሺ ሰዎች ማስተናገድ አቅም ያለው የስብሰባ አዳራሽ እና የቅርስ ሙዚየምን አካቶ የተገነባ መሆኑንም ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ማዕከሉ የቦረናን ህዝብ ባሕል፣ ታሪክ እና ፍልስፍና ለትውልድ የማሸጋገር ቁልፍ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review