AMN ሰኔ 1/2018
ህዝባችን አገልግሎት ፍለጋ ጊዜውንና ገንዘቡን ሳያባክን ያለውን ሃብት ለልማት እንዲያውል ለማድረግ ያቀድነውን ግብ በማሳካት የጀመርነውን የብልፅግና ጉዞ አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2018 ዓ.ም በሁሉም ክፍለ ከተሞች ስራ ለማስጀመር ባቀደዉና ለህዝቡ ቃል በገባው መሰረት 9 ማዕከላትን ወደ ስራ አስገብቷል፡፡
9ኛው እና ባለ 7 ወለል ህንፃ ያለዉ የየካ ክፍለ ከተማ መሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል የመንግስት አገልግሎትም በፍጥነት ተገንብቶ ተጠናቆ ለአገልግሎት በቅቷል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ ስራ የጀመረዉን የየካ ክፍለ ከተማ መሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል የመንግስት አገልግሎትን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልእክት ለህዝብ የገባነዉን ቃል በተግባር መፈጸም መለያችን ነዉ ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በሁሉም ክፍለ ከተሞች የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ፣ ፈጣን፣ ግልፅ እና ተደራሽ ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ከንቲባ አዳነች በ2018 በሁሉም ክፍለ ከተሞች ስራ ለማስጀመር ለህዝቡ ቃል በገባነው መሰረት 9 ማዕከላትን ወደ ስራ አስገብተናል ብለዋል።
የከተማ አስተዳደሩ የአገልግሎት እንግልትን እና ጉቦ የመጠየቅ ችግርን ለመቅርፍ እንዲሁም ተጠያቂነትን እና የህዝቦች በክብር የመገልገል መብትን ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ህዝባችን አገልግሎት ፍለጋ ጊዜውንና ገንዘቡን ሳያባክን ያለውን ሃብት ለልማት እንዲያውል ለማድረግ ያቀድነውን ግብ በማሳካት የጀመርነውን የብልፅግና ጉዞ አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡