የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማነት የተሰማቸውን አድናቆት ገለጹ

You are currently viewing የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማነት የተሰማቸውን አድናቆት ገለጹ

AMN – ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ፣ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት ላጠናቀቁት ለኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

የምርጫው ሂደት የኢትዮጵያውያን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት መሰረት የሆነውን ዲሞክራሲን ይበልጥ ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳየ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ሊቀመንበሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ላሳየው ሙያዊ ብቃትና ቁርጠኝነት እውቅና ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው ይፋዊ መግለጫ መሠረት፣ በምርጫው አብዛኛውን ወንበር በማሸነፍ ለላቀ ድል ለበቁት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ለብልጽግና ፓርቲ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክትም አስተላልፈዋል።

ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በአባል ሀገራት ዘንድ ተዓማኒ፣ ሰላማዊ እና ግልጽ የሆኑ የምርጫ ሂደቶችን በመከተል ዲሞክራሲያዊ አስተዳደርን ለማጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ ማረጋገጣቸውን የአፍሪካ ሕብረት ያወጣው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review