ባለፉት ስምንት ዓመታት የሀገሪቱን ዓመታዊ የሲሚንቶ ምርት ከ8 ሚሊዮን ቶን ወደ 14 ሚሊዮን ቶን ማሳደግ ተችሏል

You are currently viewing ባለፉት ስምንት ዓመታት የሀገሪቱን ዓመታዊ የሲሚንቶ ምርት ከ8 ሚሊዮን ቶን ወደ 14 ሚሊዮን ቶን ማሳደግ ተችሏል

AMN – ሰኔ 18/2018 ዓ.ም

የሲሚንቶ ምርትን ለማሳደግ በተደረገው ጥረት ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ የሀገሪቱ ዓመታዊ የሲሚንቶ ምርት ከ8 ሚሊዮን ቶን ወደ 14 ሚሊዮን ቶን በማሳደግ ገበያውን ማረጋጋት መቻሉ ተገለጸ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት፣ “ከለውጥ ወደ ዘላቂ ሽግግር” በሚል መሪ ሀሳብ የ“ኢትዮጵያ ታከናውናለች” ሀገራዊ ጉባኤ በሳይንስ ሙዚየም ተካሂዷል።

በማዕድን ዘርፍ የቀረበዉ ማብራሪያ እንደሚያመላክተዉ፤ ኢትዮጵያ ያላትን ሰፊ የማዕድን ሀብት በተቀናጀ መልክ ወደ ተጨባጭ ብሔራዊ የኢኮኖሚ ዕድገት አቅም እየቀየረች ትገኛለች፡፡

የሀገሪቱ የማዕድን ዘርፍ ቀደም ሲል ከነበረበት ደካማ አፈጻጸምና ተግዳሮቶች ተነስቶ፣ በአሁኑ ወቅት ከኢኮኖሚ ዕድገት ስትራቴጂካዊ ምሰሶዎች አንዱ መሆን ችሏል፡፡

ዉጤቱ የተገኘዉ መንግሥት በወሰዳቸው ቁርጠኛ የፖሊሲ ማሻሻያዎች፣ የገበያ ሥርዓቱን በማስተካከል እና እሴትን መጨመር በሚያስችሉ መጠነ-ሰፊ ኢንቨስትመንቶች በመታገዙ ነዉ፡፡

ሪፎርሙን ተከትሎ ማዕድንና ነዳጅን እንደ እምቅ አቅም ብቻ ከማየት ባለፈ ፣ ተጨባጭ ውጤት ወደሚያስመዘግብ ስትራቴጂካዊ አቅም እንዲሸጋገር ተደርጓል፡፡

ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ለከሰል ድንጋይ ማስገቢያ በየዓመቱ ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ ታወጣ የነበረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የሀገር ውስጥ አምራቾችንና የግል ባለሀብቶችን በማበረታታት የሀገሪቱን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ምርት መሸፈን ተችሏል፡፡

የሲሚንቶ ምርትን ለማሳደግ በተደረገው ጥረትም ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ የሀገሪቱ ዓመታዊ የሲሚንቶ ምርት ከ8 ሚሊዮን ቶን ወደ 14 ሚሊዮን ቶን በማደጉ ገበያውን ማረጋጋት ተችሏል፡፡

በወርቅ፣ በስትራቴጂካዊና ወሳኝ ማዕድናት፣ በነዳጅ እንዲሁም በማዳበሪያ ምርት ላይ እየተስፋፉ የመጡት አዳዲስ ኢንቨስትመንቶች የለውጡ ማሳያ መሆናቸው “ኢትዮጵያ ታከናውናለች” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀዉ ሀገራዊ ጉባኤ ላይ የማዕድን ሚኒስቴር ያቀረበዉ ማብራሪያ ያረጋግጣል፡፡

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review