የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሊዮን አዲስ በረራ ጀመረ

AMN- ሰኔ 24/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፈረንሳዩዋ ሊዮን ከተማ አዲስ በረራ ጀመረ።

አየር መንገዱ በሳምንት 3 ጊዜ በረራ የሚያከናውን ሲሆን፣ የመጀመሪያውን በረራውን ዛሬ ለሊት እንደሚያካሂድ ተገልጿል።

አየርመንገዱ ወደ ፈረንሳይ ሊዮን የሚያደርገውን በረራ አስመልክቶ ማምሻውን የማስጀመሪያ መርሐ ግብር አካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው፣ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር አሌክሲስ ላሜክ እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

የአዲስ አበባ እህት ከተማዋ ሊዮን የኢትዮጵያ አየርመንገድ ወደ ፈረንሳይ የሚያደርጋቸው በረራዎች ሶስተኛ መዳረሻ ከተማ ሆናለች።

አየር መንገዱ ቀደም ሲል ወደ ፓሪስ እና ማርሴይ በረራዎችን ሲያደርግ ቆይቷል።

አዲሱ የበረራ መስመር የአየር መንገዱን ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ቁጥር 146 ያደርሰዋል።

በታደሠ ሽፈራው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review