AMN-ሰኔ 24/2018 ዓ.ም

በዓለም ዋንጫው የ32 ሀገራት የጥሎ ማለፍ ዙር ቤልጂየም 2ለ0 ከመመራት ተነስታ 3ለ2 በማሸነፍ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅላለች።
ሴኔጋል ሀቢብ ዲያራ እና ኢስማኤላ ሳር ባስቆጠሯቸው ሁለት ግቦች ጨዋታውን ቢመሩም ውጤቱን አላስጠበቁም።
ቤልጂየም ሮሮሜሉ ሉካኩ 86ኛው እንዲሁም ዩሪ ቲሊሞንስ 89ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠሯቸው ግቦች ጨዋታው አቻ ሆኗል።

መደበኛው 90 ደቂቃ በዚሁ ውጤት በመጠናቀቁ ጨዋታው ወደ ጭማሪ 30 ደቂቃ አምርቷል።
በጭማሪው ደቂቃም ዩሪ ቲሊሞንስ እራሱ ላይ በተሰራ ጥፋት የተገኘውን ፍፁም ቅጣት ምት ወደ ግብነት በመቀየር በአስገራሚ ድራማ የታጀበውን ጨዋታ ቤልጂየም 3ለ2 እንድታሸንፍ አድርጓል።
ሴኔጋል ልብ ሰባሪ በሆነ መንገድ ከውድድር ውጪ ስትሆን ፤ ቤልጂየም በቀጣይ የመጨረሻ 16 ጥሎ ማለፍ የአሜሪካ እና ቦስኒያ አሸናፊን ትገጥማለች።
በሸዋንግዛው ግርማ