AMN-ሰኔ 23/2018 ዓ.ም

ቀደም ባለ ጊዜ በመሬት ላይ ያረፈን ንብረት ተሻሽጠው (ሸጠው/ገዝተው) እስካሁን የስመ-ንብረት ዝውውር ያላደረጉ (የይዞታ ማረጋገጫ) ያልያዙ አካላት በአጭር ጊዜ ሂደቱን እንዲያጠናቅቁ ጥሪ ቀረበ። የከተማ አስተዳደሩ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ መኮንን ያኢ ከኤ ኤም ኤን ዲጂታል ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት የስመ ንብረት ዝውውሩ በወቅቱ አለመደረግ ንብረት ገዝተው ነገር ግን የንብረት ባለቤት ማረጋገጫ ያልያዙ ወገኖች ለጉዳት እየዳረገ ነው ብለዋል።
የቢሮ ኃላፊው ስለ ስመ ንብረት ዝውውር ምንነት ሲናገሩም አንድ ሰው ያፈራውን ንብረት (Property) በራሱ ለሌላ ሶስተኛ ወገን የሚያስተላልፍበት ስርዓት መሆኑን ጠቅሰው የመጨረሻው ግቡም የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫን መያዝ ነው ብለዋል። ነገር ግን በተለያየ ምክንያት ይሄንን ሳያደርጉ የቀሩ እና የሚቀሩ አካላት መኖራቸውን የጠቆሙት ኃላፊው ከዚህ በፊት ሽያጭ ተሻሽጠው (ገዝተው/ሸጠው) ነገር ግን የስም ዝውውር / የይዞታ ካርታ በስማቸው ያላወጡ ባለንብረቶች ለአደጋ እንዳይጋለጡ በማሰብ መንግስት በአጠረ ጊዜ ሂደቱን እንዲያጠናቅቁ ጥሪ ያቀርባል ብለዋል።
በጉዳዩ ላይ ቢሮው የሚሰጠውን ዝርዝር መግለጫ ይዘን እንቀርባለን!!
See less