AMN- ሰኔ 27/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ግዢ ሲፈፅሙ ደረሰኝ ለተቀበሉ እና ህገ ወጥ ግብይትን ለጠቆሙ ሸማቾች እና በትምህርት ቤቶች የታክስ ክበባት ግንዛቤን በመፍጠር የአሸናፊዎች አሸናፊ ለሆኑ ተማሪዎች የሽልማትና የዕውቅና መርሃ ግብር አካሄደ።
በመርሐ ግብሩ ላይ በመገኘት ሽልማቱን ያበረከቱት የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ የሞደርናይዜሽን ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ወርቅነሽ ሰቦቃ ከተማዋን ለዜጎች ምቹ እና የተመቸች ለማድረግ ገቢን መሰብሰብ ዋና መሰረት መሆኑን አስታወሰው፣ ይህም ዜጎች የገቢ አሰባሰቡ የተሳካ እንዲሆን ሚናቸው የላቀ በመሆኑን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል ፡፡

የግብር ፍትሐዊነት ምንነትን ለማስረፅ በትውልድ ላይ በትምህርት ቤቶች መስራት ይገባል ያሉት ምክትል ቢሮ ሀላፊዋ፣ ትምህርት ቤቶች በተቋቋመ የታክስ ክበባት በታክስ ዙሪያ ለተማሪዎች ዕውቀትና ግንዛቤ ለማስያዝ ተማሪዎች የታክስ ግንዛቤን አውቀው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡
ኤ ኤም ኤን ያነጋገራቸው ዕውቅና የተሰጣቸው ሸማቾችና ተማሪዎች የታክስ ግንዛቤን ይበልጥ ማጎልበት ሃገርን ማሳደግና የዜግነት ግዴታን መወጣት በመሆኑ የተሰጣቸው እውቅና ይበልጥ በዘርፉ ላይ እንዲሰሩ አቅም በመሆኑ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
በመሀመድኑር ዓሊ