በሃገራዊ ምክክር ሂደቱ ተመካካሪዎች በአጀንዳዎች ላይ ሀሳባቸውን ያለ ገደብ እየገለጹ ነው

You are currently viewing በሃገራዊ ምክክር ሂደቱ ተመካካሪዎች በአጀንዳዎች ላይ ሀሳባቸውን ያለ ገደብ እየገለጹ ነው

AMN- ሐምሌ 18/2018 ዓ.ም

በሃገራዊ ምክክር ሂደቱ ተመካካሪዎች በአጀንዳዎች ላይ ሀሳባቸውን ያለ ገደብ እየገለጹ መሆኑን የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) ገለፁ።

ዋና ኮሚሽነሩ የምክክር ሂደቱን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ ከ10ሩ ንዑስ ቡድኖች የመነጩ ሃሳቦች ተጠናክረው ለ50ዎቹ ቡድን አባላት እየቀረቡ መሆኑን አንስተዋል።

በመዋቅሩ መሰረትም እያንዳንዳቸው 10 አባላት ያሏቸው ንዑስ ቡድኖች ሲወያዩባቸው የቆዩትን ሃሳቦች፣ አመለካከቶችና ምልከታዎች ከማመንጨት ተሻግረው ወደ ማጠናከር መሸጋገራቸውን ገልፀዋል።

ተሳታፊዎች በምክክር መድረኩ ላይ ሀሳባቸውን እያወጡ እየተመካከሩ እንደሚገኝም በመግለጫቸው አንስተዋል።

አርሶ አደሩ፣ አርብቶ አደሩ፣ አካል ጉዳተኞች፣ የተገፉ የኅብረተሰብ ክፍሎች እንዲሁም ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍሎች በመከባበር አጀንዳዎቻቸውን እያነሱ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

የሃገራዊ ምክክሩ ሂደት አበረታች መሆኑን በመግለፅ ልዩ ድጋፍ ለሚሹ የኅብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ እየተደረገ መሆኑንም አንስተዋል።

በጥንቃቄ የተደራጁና የተጠናከሩ የውይይት ውጤቶችም በአሁኑ ሰዓት በየንዑስ ቡድኖቹ ሰብሳቢዎችና ጸሃፊዎች አማካኝነት 50 ተመካካሪዎች ለያዙት ቡድኖች በንቃት እየቀረቡ መሆኑን ዋና ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

እንዲሁም ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ፣ የሃይማኖት ተቋምም ሆነ ሌላ አካል በሌላው ላይ የሐሳብም ሆነ የቁጥር ብልጫ ወስዶ ጫና እንዳያሳድር ክትትል እየተደረገ መሆኑን አረጋግጠዋል።

የሻምበል ምህረት

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review