AMN- ነሐሴ 7/2018 ዓ.ም

የሶማሌ ክልል ፕሬዚደንት ጽ/ቤት ኃላፊ ሁሴን ሀሺ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኘውን ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ጎብኝተዋል።

የሥራ ኃላፊዎቹ ከተማ አስተዳደሩ ሴቶችን ከአስከፊ ማህበራዊ ችግሮች አላቆ በልዩ ልዩ የሙያ መስኮች ለማብቃት እና እራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ የሚያከናውነውን ሰፊ ስራ በቦታው ተዘዋውረው በመመልከት አድናቆታቸውን ገልፀዋል።

ጉብኝቱ በሶማሌ ክልል ተመሳሳይ ማዕከሎችን በማቋቋም ተጠቃሚዎችን ከማህበራዊ ችግር ለማላቀቅ የሚያስችል ጠንካራ ቁርጠኝነት ለመፍጠር ትልቅ ግብ ያለው መሆኑም ተገልጿል።

የሶማሌ ክልል ፕሬዚደንት ጽ/ቤት ኃላፊ ሁሴን ሀሺ (ዶ/ር)፣ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በነገዋ የሴቶች ተሃድሶ እና የልህቀት ማዕከል የሚተገብራቸው የተሳኩ የመፍትሄ እርምጃዎች እና አሰራርሮችን በመቅሰም በክልላቸው አጠናክረው ለመተግበር የልምድ ልውውጡ የጎላ ሚና እንደሚጫወት መናገራቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።