AMN- ነሐሴ 18/2018 ዓ.ም
በካፍ የሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድን የምድብ ሁለተኛ ጨዋታውን ዛሬ ያደርጋል።
ለስድስተኛ ጊዜ እየተሳተፈ የሚገኘው ንግድ ባንክ በመጀመሪያ ጨዋታው የጅቡቲውን ኡጄኮ 11ለ0 አሸንፏል።
ዛሬ ደግሞ ከዩጋንዳው ክዋምፔ ሙስሊም ሌዲስ ጋር ይጫወታል።
በሩዋንዳ ኪጋሊ እየተከናወነ በሚገኘው በዚህ ውድድር ላይ ንግድ ባንክ ዛሬ ካሸነፈ ግማሽ ፍፃሜውን ይቀላቀላል።
ጨዋታው 11:00 ላይ ይጀምራል።
በአዲሱ መንገሻ