AMN- ጳጉሜን 05/ 2018 ዓ.ም

በምክክር ሂደቱ የተሰበሰቡ አጀንዳዎች ምክረ ሃሳቦችን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በቅርቡ የሚያስረክብ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ገልጿል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የእስካሁኑን እንቅስቃሴ እና ከዚህ በኋላ ያለውን ሂደት አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) መግለጫ ሰጥተዋል።
ዋና ኮሚሽነሩ 2018 ዓመት ፣ ኢትዮጵያዊያን በምክክር ሀገርን ለማጽናት በተወካዮቻቸው አማካኝነት በተለዩ ስምንት አጀንዳወች ላይ የመከሩበት ፣ በበርካታ አጀንዳዎችም ላይ መግባባት የደረሱበት እንደነበረ አንስተዋል።
ኮሚሽኑ በምክክር ሂደቱ የተሰበሰቡ አጀንዳዎችን ምክረ ሃሳቦች ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በቅርቡ የሚያስረክብ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) የምክረ ሃሳቦቹን ተፈጻሚነት የመከታተል ፣ ቀሪ ሂደቶችን ግልጽ የማድረግ ስራዎች የሚቀጥሉ ሲሆን የተፈለገው ውጤት እንዲመጣ ሁሉም ዜጋ ፣ ምሁራን ፣ መንግሥትና ሁሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
በምክክር መግባባት ላይ የተደረሰባቸው አጀንዳዎች በአዲሱ አመት ተግባራዊ እንዲሆኑ ዋና ኮሚሽነሩ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ቤተልሔም አየነው