AMN – መስከረም 13/2019 ዓ.ም
የቱሪዝም ሚኒስቴር ዲጂታል የቱሪስት መረጃ ማዕከልን ወደ ስራ አስገባ።
የቱሪስት መረጃ ማዕከሉ ከቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት በቅርብ ርቀት መገኘቱ በተለይ በእግረመንገድ ቱሪዝም ለተጀመረው ስራ አጋዥ እንደሚሆን የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ገልጸዋል።
የዲጂታል ማዕከሉ ኢትዮጵያን እና ውብ መስህቦቿን በአንድ ስፍራ ለመመልከት የሚያስችል መሆኑን ጠቀሰዋል፡፡
መስከረም 17 የሚከበረው የአለም ቱሪዝም ቀን የዘንድሮ መሪ ሃሳብ “ዲጂታል አጀንዳ እና ሰው ሰራሽ አስተውህሎት ለቱሪዝም አዲስ ቅኝት” የሚል መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሯ ፣ ዲጂታል የመረጃ ማዕከሉም ከዚሁ መሪ ሃሳብ ጋር የተሳሰረ ነው ብለዋል።
ከውጪ ጎብኚዎች በተጨማሪ ማዕከሉን ህፃናትና ታዳጊ ተማሪዎችን ጨምሮ ማንኛውም ሰው ቦሌ መንገድ ላይ ወደ ሚገኘው የቱሪዝም ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት በመምጣት መጎብኘት እንደሚችሉ ሚኒስትሯ ገልጸዋል።