በካናዳ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የታዳጊ ስፖርት አካዳሚ አባላት በአዲስ አበባ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ጎበኙ

You are currently viewing በካናዳ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የታዳጊ ስፖርት አካዳሚ አባላት በአዲስ አበባ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ጎበኙ

AMN- ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም

በካናዳ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የአሸናፊ ግርማ ስፖርት አካዳሚ አባላት፣ ወላጆች እና አስተባባሪዎች በአዲስ አበባ የእንጦጦ ፓርክን ጎብኝተዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞው ተጫዋች በሆነው አሸናፊ ግርማ የሚመራው ይህ የልዑካን ቡድን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች የሀገራቸውን ባህል፣ ታሪክና የተፈጥሮ ጸጋ በቅርበት እንዲያውቁ የሚያግዝና የሀገርን በጎ ገጽታ ከመገንባት ባለፈ የስፖርት ቱሪዝም ዘርፍን ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል።

የልዑካን ቡድኑ አባላት እና አስተባባሪዎች እንዲሁም የታዳጊዎቹ ቤተሰቦች በተፈጠረላቸው የትውልድ ሀገራቸውን የመጎብኘት እድል መደሰታቸውን ገልጸው፣ በተለይ በአዲስ አበባ ሁለንተናዊ የልማት ጉዞ እና ፈጣን እድገት እንደተደመሙ መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review