በኤአይ ታግዞ እየተገነባ ያለው የቢሾፍቱ አየር ማረፊያ የዘመናዊነት ማሳያ ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing በኤአይ ታግዞ እየተገነባ ያለው የቢሾፍቱ አየር ማረፊያ የዘመናዊነት ማሳያ ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN- ኅዳር 17/2019 ዓ.ም

የቢሾፍቱ አየር ማረፊያን ጨምሮ ግዙፍ የሆኑት የማዳበሪያ ፋብሪካ፣ የጋዝና ሌሎቹም ሜጋ ፕሮጀክቶች አትችሉም፣ ገንዘብ ከየት ታመጣላችሁ የሚል ጥያቄ እየተነሳ ሰርተን እያሳየን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤት አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት፣ የቢሾፍቱ አየር ማረፊያ አይነት ውስብስብና በዘመናዊ መንገድ የሚመራ ፕሮጀክት ከተወለድን አይተን አናውቅም ሲሉ ገልጸዋል።

በአንድ ጊዜ አራት ሺህ በሚጠጉ ከባድ ተሽከርካሪዎች በሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ታግዞ ሲሰራ ማየት የትራንስፖርት አስተዳደሩ በራሱ ከባድና ውስብስብ መሆኑ ማሳያ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

አሁን ላይ ቦታውን የማዘጋጀት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ስራውን በቀጣይ ሁለት ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል ብለዋል።

በቀጣይ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታውን ለመስራት የጨረታ ሂደት መጀመሩንም ጠቅሰዋል።

የቢሾፍቱ አየር ማረፊያን ጨምሮ ግዙፍ የሆኑት የማዳበሪያ ፋብሪካ፣ የጋዝና ሌሎቹም ሜጋ ፕሮጀክቶች አትችሉም፣ ገንዘብ ከየት ታመጣላችሁ የሚል ጥያቄ እየተነሳ ሰርተን እያሳየን ነው ብለዋል።

እነዚህ ግዙፍ ፕሮጀክቶች በታሰበው ጊዜ እንደሚጠናቀቁም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review