አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከኔዘርላንድ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

You are currently viewing አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከኔዘርላንድ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

AMN – ጥር 13/2017 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከኔዘርላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ስቲጅን ጃንሰን ጋር በጽ/ቤታቸው ውይይት አድርገዋል።

ውይይቱ በሁለትዮሽ ትብብር፣በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ያተኮረ እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

አምባሳደር ምስጋኑ የኔዘርላንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት እያደረጉት ያለው ተሳትፎ ተምሳሌታዊ ፋይዳ ገልጸው ፥ በመተግበር ላይ ባለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የተፈጠሩ ዕድሎችን በስፋት እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል ።

የኔዘርላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ስቲጅን ጃንሰን ኢትዮጵያ ቀጣናውን ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን የምታደርገውን ጥረት አድንቀው ኔዘርላንድስ ያላትን ድጋፍ ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review