አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ከዶናልድ ትራምፕ ጋር በነጩ ቤተመንግስት ተገናኙ

You are currently viewing አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ከዶናልድ ትራምፕ ጋር በነጩ ቤተመንግስት ተገናኙ

AMN ሰኔ 11/2017

በአሜሪካ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ጄ ትራምፕ ጋር በነጩ ቤተመንግስት የመጀመሪያ ግንኙነታቸዉን አካሂደዋል።

አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ነጩ ቤተመንግስት ሲደርሱ በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ግንኙነት የሚያንጸባርቅ ዲፕሎማሲያዊ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ይኸው ግንኙነት በቀጣይ ጊዜአት ለሚደረጉ በርካታ ውይይቶች መጠናከር ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ተብሏል።

ኢትዮጵያና አሜሪካ ከ120 ዓመታት በላይ የዘለቀ ጠንካራ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን በሁለቱ አገራት መካከል እንደ ሰላም፣ ጸጥታና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ጠንካራ አጋርነት ከመፍጠር አንጻር ያሉ ዕድሎችም ሰፊ ናቸው።

አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም በውይይቱ ወቅት የተገኙትን ስቴት ሴክሬተሪ ማርኮ ሩቢዮ ጋርም መገናኘታቸዉን ዋሽንግተን ዲሲ ከሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review