የፍሉሚኔንሱ ግብ ጠባቂ ፋቢዮ ሎፔዝ የዓለማችን የምንጊዜውም በርካታ ጨዋታዎችን ያደረገ ተጨዋች ሆነ

You are currently viewing የፍሉሚኔንሱ ግብ ጠባቂ ፋቢዮ ሎፔዝ የዓለማችን የምንጊዜውም በርካታ ጨዋታዎችን ያደረገ ተጨዋች ሆነ

AMN – ነሃሴ 14/2017 ዓ.ም

የብራዚሉ ፍሉሚኔንስ ግብ ጠባቂ ፋቢዮ ዴቪሰን ሎፔዝ በኮፓ ሱዳአሜሪካ ጨዋታ ላይ ተሰልፎ በእግር ኳስ ዘመኑ አንድ ሺ 391ኛ ጨዋታውን ማድረጉን ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል፡፡

ከፈረንጆቹ 1997 ጀምሮ የፕሮፌሽናል ጨዋታውን እያደረገ የሚገኘው የ44 ዓመቱ ሎፔዝ ከፍሉሚኔንስ ባሻገር፣ ለአትሌቲኮ ፓራኔስ ፣ ለቫስኮ ደጋማ እና ለክሩዚሮ ተጫውቷል፡፡ ከነዚህ መካከል 976 ጨታዎችን ያደገው ለክሩዜሮ ነው፡፡

አንጋፋው ግብ ጠባቂ ትናንት ለፍሉሚኔንስ 235ኛ ጨዋታውን አድርጓል፡፡ የዓለም ክብረ ወሰኖችን የሚመዘግበው ጊነስ መጽሐፍ ፤ ፒተር ሺልተን አንድ ሺ 390 ጨዋታዎችን በማድረግ ሪ ክብረወሰን መያዙን ያስታውሳል፡፡

ለብራዚል ብሄራዊ ቡድን አንድም ጨዋታ አድርጎ የማያውቀው ፋቢዮ ግን ለተለያዩ ክለቦች አንድ ሺ 391 ጨዋታዎች በማድረጉ ክብረወሰኑን መረከቡ ተነግሯል፡፡

በታምራት አበራ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review