ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ ያስመረቁት ባለ 15 ወለል ዘመናዊ የሲኒማ ማዕከል በአይነቱ ልዩና ለኪነጥበብ እድገት አዲስ ምዕራፍ ከፋች መሆኑን አበሰሩ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ ያስመረቁት ባለ 15 ወለል ዘመናዊ የሲኒማ ማዕከል በአይነቱ ልዩና ለኪነጥበብ እድገት አዲስ ምዕራፍ ከፋች መሆኑን አበሰሩ

AMN ጥቅምት 4/2018

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ ያስመረቅነው ባለ 15 ወለል ዘመናዊ የሲኒማ ማዕከል በአይነቱ ልዩና ለኪነጥበብ እድገት አዲስ ምዕራፍ ከፋች መሆኑን ሳበስር በደስታ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

መንግስት የኪነጥበብን ወሳኝ ሚና በመረዳትና ልዩ ትኩረት በመስጠት በቢሊዮኖች በጀት መድቦ በአይነታቸው ልዩና ዘመናዊ ለሲኒማ ፣ለቲያትር ራሳቸውን የቻሉ ትልልቅ ማዕከላት ሲገነባ ፤ በኪነጥበብ ዘርፈ የተሰማራችሁ ከያኒያንና የጥበብ ቤተሰቦች ሁሉ፣ ለአገራችን ሁለንተናዊ ብልጽግና መረጋገጥ መሰረት የሚሆኑ የጥበብ ስራዎችን በማበርከት፣ ታሪክ የማይዘነጋው ዘመን ተሻጋሪ አስተዋጽኦ እንደምታበረክቱ በማመን ነው ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review