የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከአጋር ሀገራት እና ተቋማት ጋር የውይይት መድረክ አከሂዷል።
በመድረኩ የምክክሩን ሂደት በተመለከተ ለአጋር አካለቱ ገለጻም ተደርጓል።
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርዓያ (ፕ/ር) የኮሚሽኑን ስራ እየደገፉ ላሉ አጋር ሀገራት እና ተቋማት ምስጋና አቅርበዋል።
በቀጣይ ለሚኖሩ የምክክር ምዕራፎች የአጋር አካላት ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪም አቅርበዋል፡፡
በመድረኩ የታደሙ የአጋር ሀገራት ተወካዮች በሰጡት አስተያየት እስካሁን የተከናወኑ ተግባራት ሀገራዊ ምክክሩ ከህልምነት ወደ እውነታነት እንዲሸጋገር ያስቻሉ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የተጀመሩ አበረታች ስራዎች የበለጠ ፍሬያማ እንዲሆኑም የሚያደርጉትን ትብብር እና ድጋፍ እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል ሲል ኮሚሽኑ ለኤ ኤም ኤን የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡