ከኅዳር 28 ጀምሮ ሲካሄድ የቆየውየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የክለቦች፣ ታዳጊዎች፣ የግል ተወዳዳሪዎች እና የቀድሞ ብስክሌተኞች ውድድር ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡
ውድድሩ በከተማ አስተዳደሩ የተገነቡ የኮሪደር ልማቶችን ለማስተዋወቅ እና ለኅብረተሰቡ ግንዛቤ ለመፍጠር እንዲሁም በተለያዩ ዘርፎች ከተማ አስተዳደሩን የሚወክሉ ስፖርተኞችን ለመምረጥ ዓላማውን አድርጎ ተከናውኗል፡፡
በማውንቴን ታዳጊ ሴቶች ሀና ተሻለ ቀዳሚ የአጠቃላይ አሸናፊ ስትሆን፣ አሳንቲ ቦሪ እና ቤተልሔም ተስፋዬ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ሆነው አጠናቀዋል፡፡
በማውንቴን አዋቂ ሴቶች ሀዊ ደሪባ ቀዳሚ ሆና ስታጠናቅቅ ሮማን አብዮት እና አስቴር መገርሳ ተከታትለው ገብተዋል፡፡

በኮርስ አዋቂ ሴቶች ማርታ ካሳሁን፣ ሌሎ ሁንዴ እና ማለፊያ ሽፈራው በቅደም ተከተል ከ1-3 ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል፡፡
በማውንቴን ታዳጊ ወንዶች ሚሊዮን ብዙነህ ፣ ያሬድ መላኩ እና ቤካ ወ/ኪዳን ተከታትለው ገብተዋል፡፡
በማውንቴን አዋቂ ወንዶች ደግሞ ጵንኤል አባተ ቀዳሚ ሆኖ ሲያጠናቅ የአብስራ ግርማ እና ሀቢብ ሀይደር ሜዳልያ ውስጥ ገብተዋል፡፡
በቀድሞ ብስክሌተኞች አጠቃላይ አሸናፊ ቢንያም መርዕድ ቀዳሚ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ሀብቶም ካሕሳይ እና ምራቸው ለማ ተከታትለው ገብተዋል፡፡
በኮርስ ወንዶች በግል ድምር ሰዓት ብርቱ ፉክክር በታየበት ውድድር አጠቃላይ አሸናፊ ዮሐንስ ታሪኩ ከሸገር ብስክሌት ክለብ ቀዳሚ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ሰለሞን ዓለሙ እና አዕምሮ መንግስቱ ከአ.አ ፖሊስ ብስክሌት ክለብ ተከታትለው ገብተዋል።
በክለቦች ድምር ሰዓት ሸገር ከተማ ቀደሚ ሆኖ ሲያጠናቅቅ አ.አ. ፖሊስ እና የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ 2ኛ እና 3ኛ ሆነው ውድድራቸውን አጠናቀዋል፡፡
በአጠቃላይ ከ1-3 ለወጡ ብስክሌተኞች ከ75,000 ብር በላይ ሽልማት እንዲሁም ዋንጫ እና ሜዳሊያ ተበርክቶላቸዋል፡፡
በዓለማየሁ ሙሳ