የከተራና ጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር ወጣቶች የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ጥሪ አቀረበ

You are currently viewing የከተራና ጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር ወጣቶች የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ጥሪ አቀረበ

AMN ጥር 8/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ከአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር የጃንሜዳ ታቦት ማደሪያን የማጽዳት መርሀ ግብር አካሂዷል።

የከተራና ጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በአደባባይ ከሚከበሩ በዓላት ቀዳሚው በዓል ነው፡፡

ይህንን በዓል ምክንያት በማድረግም በየዓመቱ ታቦታቱ የሚያድሩባቸው ቦታዎች ይጸዳሉ ፡፡

የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበርም ከአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር የጃንሜዳ ታቦት ማደሪያን አጽድተዋል።

የጽዳቱ ተሳታፊዎችም የጥምቀት በዓል በዓለም ቅርስነት የተመዘገበ ሀይማኖታዊ በዓል ሲሆን ለበዓሉ የተከናወነው የጽዳት መርሀ ግብርም ሀገራዊ አንድነት የሚንጸባረቅበት ነው ብለዋል ፡፡

ወንድማማችነትና እህትማማችነት ኢትዮጵያዊ መገለጫ መሆኑን ያነሱት የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ክብርዓለም ደምሴ አብሮነትና አንድነትን በማንጸባረቅ በኩል ወጣቱ ሁነኛ ማሳያ መሆን እንደሚገባም ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበርም ወጣቶች በተለይ የአደባባይ በዓላት ሲከበሩ ሚናቸውን ሲወጡ ስለመቆየታቸው አንስተው መጪው የከተራና ጥምቀት በዓልም ትውፊቱና ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር ወጣቶ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ በረከት ብርብርሳ አሳስበዋል።

በጽዮን ማሞ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review