በአውቶብስ ተንቀሳቃሽ የመሶብ አገልግሎት ሊጀመር ነው

You are currently viewing በአውቶብስ ተንቀሳቃሽ የመሶብ አገልግሎት ሊጀመር ነው

AMN – ጥር 26/2018 ዓ.ም.

አውቶብስን በመጠቀም ተንቀሳቃሽ የመሶብ አገልግሎት ሊጀመር መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት የመንግሥትን የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም በሚመለከት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ ነው፡፡

የመሶብ አገልግሎት መስጫዎች 33 መድረሳቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የማዕከላቱ ቁጥር በዚህ ዓመት 100 እንደሚደርሱ ተናግረዋል።

ሲስተም በማበልጸግ እየተሠራ በመሆኑ በዓመት ውስጥ 100 ቨርችዋል አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት መገንባት ትልቅ እመርታ መሆኑን ነው የጠቀሱት፡፡

አግልግሎቱን በተቋም ደረጃ ማዳረሱ በቂ ስላልሆነ፣ ተንቀሳቃሽ የመሶብ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል በአውቆብስ ቨርቹዋል መሶብ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። ወደ ተግባር ለመግባትም ሶስት ወራት እንደሚፈጅ ነው የገለጹት፡፡

አገልግሎቱ ሲጀመር በየአካባቢው በመንቀሳቀስ እሑድ ጭምር ራቅ ባሉ አካባቢዎች ማዳረስ የሚያስችል እንደሆነ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕዝቡን ሮሮ ለመቀነስ፣ የመፈጸም ብቃትን ለማሳደግና ሌብነትን ለመቀነስ እንጠቀምበታለን ብለዋል።

በታደሰ ሽፈራው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review