ከሻዕቢያ ጋር ጸቡ ጫፍ የደረሰው የፕሪቶሪያ ስምምነት ሲፈረም መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናገሩ

You are currently viewing ከሻዕቢያ ጋር ጸቡ ጫፍ የደረሰው የፕሪቶሪያ ስምምነት ሲፈረም መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናገሩ
  • Post category:ፖለቲካ

AMN ጥር 26 ፣ 2018

አንዳንዶች በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ችግር የተፈጠረው መንግስት የቀይ ባህር ጥያቄ ስላነሳ ይመስላቸዋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አብራርተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የመንግሥትን የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም በሚመለከት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ በሀገራት መካከል ስለነበረው ግጭት አብራርተዋል፡፡

በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ችግር የተፈጠረው መንግስት የቀይ ባህር ጥያቄ ስላነሳ ነው ብለው የሚገልጹ ቢኖሩም አለመግባባቱ በሰሜኑ ወጊያ ወቅት የነበረ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ኤርትራ ከተፈጠረች ጀምሮ በሁለቱ መንግስታት መካካል ችግሮች ነበሩ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ የለውጡ መንግስት አያስፈልግም በሚል ወደ ሰላማዊ ሁኔታ ለመመለስ መሞከሩን ነው የገለጹት፡፡

“አምስት አመታት ሙሉ ሰንለምን ቆይተናል “ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

“በትግራይ በነበረው የመጀመሪያው ዙር ውጊያ ሽሬን ስናስለቅቅ የኤርትራ ጦር ከኋላ ገብቶ የአንዳንድ ሰዎችን ቤት ፎቅ ማፍረስ ሲጀምር ጸቡ ያኔ ተጀመረ አልተናገርነውም እንጂ፡፡” ሲሉ ጠቅሰዋል፡፡

የፕሪቶሪያ ስምምነት ሲፈጸም ፣ የኤርትራ መንግስት እንዴት የሰላም ስምምነት ተፈረመ በሚል አቋም ጫፍ ወደ ረገጠ ጸብ መግባቱን አንስተዋል፡፡

ከዚህ ኃይል ጋር ነው ህውሃት ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየሰራ ያለው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ዛሬ የህውሃት አንዳንድ አመራሮች ያላቸውን አቋም ሳይ ምን ያክል ህዝባቸውን እንደሚጠሉ የህዝባቸው በደል እደማይሰማቸው ነው የሚገባኝ በማለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

ታደሰ ሽፈራው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review