AMN- የካቲት 12/2018 ዓ.ም
89ኛው የካቲት 12 የሰማዕታት መታሰቢያ ቀን በአዲስ አባባ በተለያዮ ሁነቶች እየታሰበ ይገኛል።
የዛሬ 89 ዓመት ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት አብርሃም ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶም በጦር አዛዡ ሩዶልፍ ግራዚያኒ ላይ ቦንብ ወርውረው ጉዳት ማድረሳቸውን ተከትሎ፣ የጣሊያን ጦር የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም 30 ሺህ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በግፍ መጨፍጨፉን ታሪክ ይነግረናል፡፡

የአባት አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን ባደረጉት ንግግር፣ የአባቶቻችንን ተጋድሎ ስናስታውስ የኢትዮጵያውያን ቅኝ ገዥዎችን አንገት ያስደፋ ተጋድሎ ለዛሬው ትውልድ ስንቅ ነው ብለዋል።
መታሰቢያ ቀኑን ስናከብር የአባቶችን የተጋድሎ ክብር በሚመጥን መልኩ ታሪክን በመሰነድ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።

በመታሰቢያ መርሐ-ግብሩ ህፃናት፣ ወጣቶች፣ እናትና አባት አርበኞች እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለድርሻዎች ተገኝተዋል።
በንጉሱ በቃሉ