AMN- ሚያዝያ 01/2018 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ፣ የቡሩንዲ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኤቫሪስቴ ንድያይሺሚዬ፤ በድንቅ ህዝቦቿና ባህሏ ወደ ምትቀበሎት ሀገሬ ኢትዮጵያ እንኳን በሰላም መጡ ስል በታላቅ ክብር ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ ጥልቅ የሆነ የወንድማማችነት እና የጋራ መከባበር ታሪክ ያላቸው መሆኑን ያጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዘላቂ ትስስርም በከፍተኛ ሁኔታ እንደምናከብር ላስታውሶት እወዳለሁ ሲሉ ገልጸዋል።

በዚህ ይፋዊ የስራ ጉብኝትዎ፣ ለወደፊቱ ያለንን የጋራ ትልም ወደ እውነት ለመቀየር በምናደርገው ጥረት፤ ቆይታዎ ግንኙነታችንን የበለጠ እንደሚያጠናክረው አልጠራጠርም። በድጋሚ እንኳን ወደ ሁለተኛ ቤትዎ በደህና መጡ ለማለት እወዳለሁ! ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡