AMN- ሚያዝያ 01/2018 ዓ.ም
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ፣ ዛሬ የቡሩንዲ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ-መንበር ኢቫሪስት ንዴሺሚዬን በአድዋ ድል መታሰቢያ በክብር ተቀብለናቸዋል ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ በአድዋ ጀግኖች መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን ያኖሩ ሲሆን፤ ለመላው ጥቁር ህዝቦች የነፃነት ፋና ወጊ የሆነውን የአድዋ ድል ታሪክም አስጎብኝተናቸዋል ሲሉ ጠቅሰዋል።

በአድዋ ድል መታሰቢያ ለነበረዎት ቆይታ እያመሰገንኩ፤ በምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ እንዲሁም በአፍሪካውያን ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ የሚኖርዎት ቆይታ ፍሬያማ እንዲሆን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም እመኛለሁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።