የአለምን ጉሮሮ የዘጋችዉ – ሆርሙዝ ተከፈተች

You are currently viewing የአለምን ጉሮሮ የዘጋችዉ – ሆርሙዝ ተከፈተች

AMN – ሚያዝያ 09/2018 ዓ/ም

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆርሙዝ ወሽመጥ ለቀሪው የተኩስ አቁም ጊዜ ሲባል ለንግድ መርከቦች ሙሉ በሙሉ ክፍት መደረጉን መግለጻቸዉን ተከትሎ በርካቶች ደስታቸዉን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ፡፡

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራቅቺ፣ የሆርሙዝ ወሽመጥ ለቀሪው የተኩስ አቁም ጊዜ ሲባል ሙሉ በሙሉ ክፍት መሆኑን አውጀዋል፡፡

ውሳኔዉ በእስራኤልና በሊባኖስ መካከል የተደረገዉን የተኩስ አቁም ተከትሎ የመጣ ሲሆን፤ ሆርሙዝ ወሽመጥ ለሁሉም የንግድ መርከቦች ሙሉ በሙሉ ክፍት መሆኑ ታውጇል።

የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ ማህበራዊ የትስስር ገጻቸዉ እናመሰግናለን ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ከኢራን መግለጫ በኋላ የነዳጅ ዋጋ ወዲያውኑ መቀነሱ ተነግሯል፡፡

ኢራን ይህንን መግለጫ ያወጣችው ዩናይትድ ኪንግደም እና ፈረንሳይ በወሽመጡ ላይ ያለውን የመርከብ ነፃነት ለመወያየት ከሌሎች በርካታ አገራት ጋር ስብሰባ እያካሄዱ ባሉበት ወቅት ነው፡፡

ኢራን የአለምን ጉሮሮ የዘጋውን ሆርሙዝን የከፈተችዉ ቀደም ብሎ በእስራኤል እና በሊባኖስ መካከል የ10 ቀናት የተኩስ አቁም መጀመሩን ተከትሎ መሆኑ ክስተቱን ልዩ አድርጎታል፡፡

ቤሩት የተኩስ አቁም ስምምነቱን በደስታ እያከበረች መሆኗን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ኢራን በእስራኤል እና በአሜሪካ ለተሰነዘረባት ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ስትል የዓለማችንን የነዳጅ ማጓጓዣ መስመር ለሳምንታት ዘግታው ቆይታለች፡፡

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review