AMN-ሰኔ 16/2018 ዓ.ም

እንግሊዝ እና ጋና በምድብ 12 ያከናወኑት ጨዋታ 0ለ0 ተጠናቋል።
በቦስተን ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ እንግሊዝ እንደተጠበቀው በኳስ ቁጥጥር ብልጫ ብትወስድም ግልፅ የማግባት ዕድል መፍጠር ግን አልቻለችም።

ጋና እንደ ቡድን የመከላከል አቅሟን ብታሳይም በማጥቃቱ ተዳክማ ታይታለች።
እንግሊዝ የዛሬውን ጨምሮ በዓለም ዋንጫው ታሪክ 13 ጨዋታዎችን 0ለ0 ያጠናቀቀች ብቸኛዋ ሀገር ሆናለች።

በመጀመሪያ ጨዋታዋ ክሮሺያን ያሸነፈችው እንግሊዝ አራት ነጥብ ይዛለች። ፓናማን አሸንፋ ውድድሯን የጀመረችው ጋናም በተመሳሳይ አራት ነጥብ አላት።
እንግሊዝ በቀጣይ ፓናማን ስትገጥም ፣ ጋና ከክሮሺያ ትጫወታለች።
በሸዋንግዛው ግርማ