
AMN ህዳር 17/2017 ዓ .ም
የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን መከበሩ የኢትዮጵያ ፀጋ የሆኑት ብዝሀነት፣የግልና የቡድን መብቶች እንዲከበሩ፣ በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ ህብረ ብሔራዊ አንድነት እንዲጎለብትና ስር እንዲሰድ አስችሏል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ገለጹ።

19ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል “ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሀሳብ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በድምቀት ተከብሯል።
በበአሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን መከበሩ የኢትዮጵያ ፀጋ የሆኑት ብዝሀነት፣ የግልና የቡድን መብቶች እንዲከበሩ፣ በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ ህብረ ብሔራዊ አንድነት እንዲጎለብትና ስር እንዲሰድ አስችሏል ብለዋል።
አዲስ አበባ ከተማን በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በማስተሳሰር ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራታቸውንና የከተማዋን ሀብት በፍትሀዊነትና በእኩልነት ማልማት እንደተቻለ መናገራቸውን ከክፍለ ከተማው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።