ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ አቭዬሽን ሴኩዩሪቲ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን አፀደቀ

You are currently viewing ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ አቭዬሽን ሴኩዩሪቲ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን አፀደቀ

AMN- ሚያዚያ 13/2018 ዓ.ም

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ስብሰባ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ሴኩዩሪቲ አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አጸደቀ፡፡

በምክር ቤቱ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ፈቲህ መሀዲ (ዶ/ር) ረቂቅ አዋጁን አስመልክቶ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡

የማሻሻያ አዋጁ በሚዘረጋቸው አሠራሮችና ቴክኖሎጂዎች መሠረት ያሉትን የደህንነት ስጋቶች የሚፈታ ስለመሆኑ በውሳኔ ሀሳቡ ተገልጿል፡፡

በዓለም አቀፍ የሲቪል አቭዬሽን ስታንዳርድና መለኪያ መሠረት የተሻለ የአቭዬሽን ሴኩዩሪቲ መገንባት የሚያስችል እንዲሁም፤ እንደ ሀገር ከዚህ በፊት የነበረውን መልካም ገጽታ ለማስቀጠል የሚያስችል ማሻሻያ አዋጅ ስለመሆኑም ምክትል ሰብሳቢ ፈቲህ (ዶ/ር) አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ እንደ ሀገር ሲያስመዘግብ የነበረውን ከፍተኛ ውጤት ለማስቀጠል ወቅቱን የዋጀ የሕግ ማዕቀፍ በማበጀት ለዓለም ማህበረሰብ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ አስተማማኝና ቀልጣፋ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችልም ተብራርቷል፡፡

ነባሩ አዋጅ 432/1997 ከ20 ዓመታት በላይ ያለማሻሻያ የቆየ በመሆኑ ዘመኑ ያመጣቸውን ውስብስብ ሕገ ወጥ ጣልቃ ገብ ድርጊቶችን ለመቆጣጠር የሚያስችል ስለመሆኑም ተገልጿል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት በበኩላቸው የአዋጁን አስፈላጊት በሚመለከት አስተያየት ያቀረቡ ሲሆን፤ በቀጣይ ገቢ አሰባሰብን ጨምሮ አፈፃፀም ላይ ትኩረት ሊደረግ ይገባል ያሏቸውን ሀሳብ አቅርበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review